Tumgik
#አንባቢ
Photo
Tumblr media
#አንባቢ አይሰርቅም #bahirdar #tanadar https://www.instagram.com/p/B6jtMenAUUA/?igshid=wmzutb4npp6n
0 notes
hornaffairs · 7 years
Photo
Tumblr media
የኦሮሞ ብሔርተኝነት ከኢትዮጵያዊነት አይጣላም! (ኤቢሳ ከጨፌ ዶንሳ) ስለ ሀገርና ህዝብ ፍቅር የሚናገር ማንም ቢሆን የኋላ ታሪክን ጠንቅቆ ከማወቅ፤ ያሁኑን አጠቃላይ ሁኔታ ከማገናዘብና መጪውን ጊዜ በትክክል ከመተንበይ ቢነሳ የሚሻል የሆናል ስል አሰብኩ፡፡ በርግጥ ትክክል የሚባለው አስተሳሰብ አንፃራዊና ከማህበረሰብ እድገት ጋር ተለዋዋጭ ሁኔታን የሚከተል ቢሆን አይገርምም፡፡ በዚሁ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ተጨባጩን ሁኔታ ያገናዘበ አተያይን መከተል የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ባሻገር በአንድ አስከፊ ወቅት በተፈጠረ ሰንካላ አስተሳሰብና ድርጊት ላይ ብቻ በመመርኮዝ ሀገርና ህዝብን መፈረጅ እንዲሁም ጠባሳው እንዳይሽር ማድረግ አጠቃላዩን ዘመን ማጨለም ይሆናል፡፡ ምናልባትም ከዚያ አስከፊ ገፅታ በኋላ ህዝብም ሆ�� ሀገር የሰራው አኩሪ ታሪክ ይኖር ይሆናልና ከመወሰን ቀድሞ እንዚያን ሁኔታዎች መመርመር አስፈላጊ ይሆናል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ አብዛኞቹ ፀሀፍት በተለይ ዛሬ ዛሬ እየተግባቡበት እንደመጡት የዴሞክራሲን ፅንሰ ሀሳብ በተግባር ለዓለም ከማስተማር ባለፈ ከመሰል ህዝቦች ጋር በጋራና በአንድነት፤ በመፈቃቀድና በመከባበር እንዴት ይኖር እንደነበረ ሲታሰብ ሀገርንም ሆነ ህዝብን የመገንባት ታሪካዊ እሴት ያዳበረ ህዝብ እንደሆነ ምርምሮቻችንና ጽሑፎቻችን አስረጅ ናቸው፡፡ ስለ አብሮ መኖርና አንድነት እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያዊነት ስናገር፤ አንዳንዶቹ መንፈስ አንዳንዶችም የክፋት ካባ አድርገው እንደሚስሉት እንዳይደለ ከወዲሁ አንባቢ ቢረዳኝ እሻለሁ፡፡ እኔ የማወራው ህዝቦች ያለመነቃቀፍና ያለመደነቃቀፍ አንገታቸውን እኩል ቀና አድርገው ስለሚኖሩባት፤ ሁላቸውም አቅማቸው በፈቀደ መጠን ባደረጉት ጥረትና በላባቸው ውጤት ተጠቃሚ ስለሚሆኑባት፤ ፍትሀዊ የተፈጥሮ ሀብት ክፍፍልን ያስተናገደችና መሰረታዊ የህገመንግስትና የፌዴራል ስርዓቱን መርሆዎች ለዜጎቿ ማክበር ስለምትችለዋ ኢትዮጵያ ነው፡፡ ይህቺ ሀገር ደግሞ በሁላችን ፈቃድና መተማመን የምትገነባ እየተገነባችም የምታብብ ሀገር ናት፡፡ ነሸጥ ያረገው በአንድ ጀንበር ተነስቶ የሳላት ወይም የሚስላት ንግርትም አይደለችም፡፡ በህዝቦች እውነታ፤ ፍትሀዊና፤ እኩል አብሮ የመኖርና የማደግ ተግባር ውስጥ የምትከሰት እንጂ፡፡ የኦሮሞ  ብሔርተኝነት ከመሰረቱ ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊነት ደግሞ የራስ መብትና ጥቅምን ከሌሎች መብትና ጥቅም ሁሉ እኩል ለማስጠበቅ የሚታገል ነው፡፡ ራስን አጓጉል ወዶ ሌላውን የሚያሳንስ አይደለም፡፡ ለራስ ሲሞላ ለሌላው እንዲጎድል መሻት አይደለም፡፡ የሌላንም እድል ቀምቶ የራስ ማድረግ አይደለም፡፡ ባለኝና በፈጠርኩት እድል ልክ እንድኖር ማንንም ማስፈቀድ የለብኝም፤ መብቶቼ በእጆቼና በህገመንግስቱ ጥላ ስር ናቸው ባይ እንጂ! ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ ከዚህ ባሻገር ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኝነት በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር በመሸሸግ ሳይሆን ጎልቶና ጎልብቶ ኢትዮጵያዊነትን የሚያዳብር ስለመሆኑ የሚከራከሩ ሁለት ፅንፍ አስተሳሰቦች አግራሞት ይፈጥሩብኛል፡፡ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ባለ ዛሮች ከሰሞኑ ከተዳፈኑበት ወጥተዋል፡፡ ይህ ምንም ጥያቄ የሌለው የማያከራክርም የባላባቶቹን የመሳፍንቱ የአንድ ድንበር፤ ባንዲራና ቋንቋ አቀንቃኞች መንፈስ መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡ ሌላኛው ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ካለፈው ጠባሳ ያለመሻርና መሸሽ አድርገው የሚስሉቱም ስሙን እትጥሩብን ባዮች ናቸው፡፡ ሁለቱም ለኦሮሞም ሆነ ለሌሎች ወንድም ህዝቦች አይጠቅሟቸውም፡፡ አንደኛው ሞቶ ከተቀበረ ሁለት አስርት ያሳለፈ፤ ሌላኛውም ቢሆን ጠባሳውን ለማከክ ካልሆነ በስተቀር ትውልድ ያለፈውና ህዝባችን በዚህ ድርጊትና ጠባሳ ላይ ሌላ የሰላምና የመፈቃቀድ ሀውልት ያቆመበት ከመሆኑ አንፃር  ጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ፈረሶቹን፤ ጋሻና ጦሩን፤ የድል አድራጊነት ወኔውን ባንድ ላይ አድርጎ አድዋ ሲዘምት ጣሊያንን ድባቅ በመምታት የዚህ ሀገር በቀል ህዝቦች ምድር እንዳትደፈር ብቻ ሳይሆን ስርዓቱ እየፈጠረ በነበረው ጠባሳ ላይ የአብሮነት የመፈቃቀድና የእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አብሮነት ሀውልት እየገነባ ነበር፡፡ 5 ዓመት በዱር በገደሉ ከጣሊያን ጋር ሲተናነቅም የኮበለሉት የስርዓቱ ቁንጮ ቂቤ ቀብተውት እንዳልሆነ አጥቶ ሳይሆን ህዝቦች በጋራና በእውነተኛ አንድነት መኖር ከቻሉ የማትደፈር ሀገር ሊኖረን እንደሚችልና ይህንንም በራሱ መስዋእትነት መገንባት እንደሚቻል በተጨባጭ ማሳየቱ ነበር፡፡ እልፍ ሲልም ከታላቁ የኩሽ ነገድ የተገኙ ህዝቦች ለግሪካውያን በተጣመመ ምእራባዊ አስተሳሰብ የተሰጠውን የዓለም ስልጣኔ መንበር ቀድሞ እንደተቀመጠበት የሚያረጋግጠው ታሪክ የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ ሀገር ባሻገርም ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ስልጣኔ ያበረከታቸ��� ሰልጡን ባህላዊ እሴቶች ባለቤት እንደሆነ፤ ከዚህ መለስ ደግሞ በሀገር ውስጥ ያልተዘመረለት ህዝብ ሆኖ እንዲቆይ የተገደደበትን ሁኔታ ወደትክክለኛው ሚዛን በመመለስ የመፈቃቀድ ኑሮን የሰበከ ህዝብ ስለመሆኑ  አስታዋሻችን ነው፡፡ ይህ ታሪክ ታሪካችን ነው፡፡ ይህ ሀቅ ሀቃችን ነው፡፡ ይህንን መካድ ሲጀመር ብቻ ነው የሌለና ከተቀበረ ዘመናት የቆጠረ መንፈስም ሆነ በክፋት ካባ የተሳለ ጠባሳን አመርቃዥ አስተሳሰብ ሆኖ የሚከሰተው፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ  ብሔርተኘነት በምንም መሰረታዊ ነጥብ ከኢትዮጵያዊነት አይጣላም፡፡ አንድ የፌስቡክ ገፅ ፀሀፊ እንዳለው የዚህ ህዝብ ጥያቄ በኢትዮጵያዊ ማንነት ትርክት ላይ እንግባባ ነው፡፡ የሌለና ሊኖር በማይችል ትርክት ሳይሆን ከህዝብ የአኗናርና የልባዊ ፍላጎት ታሪካዊ ዳራ በመነሳት የዛሬይቱን የጋራ ሀገር እንስራ ነው፡፡ ተሰርታ ያለቀች ህንፃ አድርገው የሚያስቧትም ሆነ ፍርስርሷ ብቻ ሲወጣ ነው መልሴ የሚሉቱ ቦታ አላቸው ብዬ ማሰብ ይከብደኛል፡፡ ይልቅስ በዚህ ሀገር ሁሉም ህዝቦች ታላቅ፤ ሁሉም ህዝቦች ተጠቃሚ፤ ሁሉም ህዝቦች ፍትሀዊ የሀብት ባለቤትና የስርዓቱ አባቶች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በተፈጥሮ ያገኙትም ሆነ ዘመን ያመጣው መብት የትኛውንም ህዝብ ሊነፈግ አይገባም፡፡ ሰጪም ነሺም ማንም ሊሆንም አይችልም፡፡ ያለፈ፤ አሁን ያለንናና ነገ የሚኖረንን ህብር መተንበይ የሚችል አእምሮ የኦሮሞን ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ከኢትዮጵያዊነት አያጣላም፡፡ ከዚህ የሚገኝ ትርፍ ብተናና መተላለቅ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የኦሮሞን የዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ልሂቃንም ሆነ ምልዓተ ህዝቡን በሞተ መንፈስ ማጥመቅ የሚታትሩ፤ የኢትዮጵያዊነትን ማንነትን እነእንቶኔ ከፈጠሩት ጠባሳ በማዋደድ አንዳልሻረ አሊያም ሊሽር እንደማይችል የሚያደርጉቱ የማን ጠበቆች እንደሆኑ ገሀድ እየወጣ መጥቷልና በኛ አይነገድ እላለሁ፡፡ **********
0 notes
ethioexplorer · 8 years
Photo
Tumblr media
“እኛና ልጆቻችን!” – ኤርሚያስ ለገሰ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ያሆነኝ ባለፉት ጊዜያቶች “የለውጥ ሐይሎች ግልጽና ደፋር ውይይት ለመፍትሄና የጋራ ድል” በሚል ርእስ ተዘጋጅተው ከተሰራጩት ግብረ-መልሶች በመነሳት ነው። መጣጥፎቹ ከቀረቡና በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ላይ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ ሃሳቡን በመደገፍም ሆነ በመቃወም የተለያዩ አስተያየቶች ተሰ��ተዋል። በተደጋጋሚ እንደተጠቆመው ከተራ ስድብ ባሻገር የቀረቡትን ሃሳቦች በሙሉ ከፍተኛ አክብሮት የሚሰጣቸው ናቸው። የተፈለገውም “ግልጽና ደፋር ዉይይት” ማድረግ ስለሆነ አላማው በከፊል እንደተሳካ ሊወሰድ የሚችል ነው።ሙሉ ለሙሉ ተሳክቷል ለማለት አፌን ሞልቼ መናገር ስላልቻልኩ ነው። ለሁሉም እንደሚታየው አንድ መጣጥፍ ለህዝብ ሲቀርብ የተወሰነውን አንባቢ ያስደስታል። ከፊሉን ምንም ትርጉም አይሰጠውም። ግማሹ ደግሞ ከመናደድ አልፎ ጸሃፊውን አግኝቶ ለመተናኮል ያስባል። የኢትዮጵያን ችግር መፍትሄ አንዲት ገጽ ጻፍ ቢባል እንደ ሎጥ ሚስት የሚሆነው ሌሎች ባቀረቡት ላይ ቡጡ ካልተሰረዝኩ ይላል። ስሙን በደበቀበት ፌስቡክ ለጽሁፍ አቃቂርና ለንግግሩ ለናቲካ ለማውጣት ይሯሯጣል። ሙሉ ለሙሉ ተሳክቷል ያላልኩት እንደዚህ አይነት ትናንሽ ሰዎች በየቦታው በመኖራቸው ነው። አብዛኛው ህዝብ ግን በችኮላና ስሜታዊነት ሳይሆን በጥንቃቄ እውነቱን መርምሮ ለመረዳት በመፈለጉ ትልቅ ጉልበት ሰጥቶኛል።
0 notes
hornaffairs · 7 years
Photo
Tumblr media
የዘዉጌ ዋልተኝነት (Ethnic Polarization) እና የኢትዮጵያ አደገኛ ሁኔታ (ይታገሱ ዘዉዱ) ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው በመመረጣቸው ደስ በሎኛል፡፡ ለምን ቢባል የአገሬ ሰዉ ናቸዉ…………. ኢትዮጲያዊ …… ወዲህም ጥቁር አፍሪካዊ! የደስታየም ምክንያት ጥቁር አፈር ያበቀላቸዉ የጥቁር ህዝብ ልጅ በመሆናቸዉ ብቻ ነዉ ፡፡ ጥቁር በአለም መድረክ ላይ ከፍ ከፍ ሲል ደስ ይለኛል፡፡ ነጮቹ እንደሚሉት የጥቁር ዘረኛ  (Black-ish ) የመሆን ጉዳይ አይደለም ፡፡ ጥቁር ህዝቦች ለበርካታ ዘመናት ግፍ ተፈጽሞባቸዋል …….በባርነት ተግዘዉ በደምና በላባቸዉ ባቆሙት አገር ላይ ዛሬም ድረስ ከዉሻ አንሰዉ በየአደባባዩ በዘረኛ ነጮች ደማቸዉ ይፈሳል፡፡ ጥቁር አፍሪካዉያን በቅኝ ተገዝተው በገዛ መሬትና ሃብታቸዉ  ላይ ነጭ እንዳሻዉ ሲጭን ሲጋልብቸው ኖሯል፡፡ ዛሬ በመላዉ አፍሪካ ላለዉ አስከፊ ድህነት፣ ማህበራዊ ቀዉስ፣ ዘረኝነት፣ የስነ-ልቦና መዳሸቅ፣ የስነም-ግባር መዘቀጥት፣ አንባገነናዊ ስርዓት መፋፋት፣ ማባርያ ለሌለዉ የእርስ በርስ ጦርነት፣ አዋራጅ ስደት፣ ስፍር ቁጥር ለሌለዉ የጥቁር ህዝብ ስንክ ሳር ከቀኝ ገዥዎች ሰንኮፍ (colonial legacy) ቀድሞ ሊጠቀስ  የሚችል ነገር ከቶ ��ምን ሊኖር ይችላል? ስለሆነም ጥቁር በአለም አደባባይ የፊት ገጽ ላይ በመልካም ስም እና ስብእና በመዓረግ ሲገለጽ ደስ ይለኛል! እንኳንስ ለአገሬ ሰዉ ሊያዉም በግሌ ትህትናዉ ለሚማርከኝ ኢትዮጵያዊ ይቅርና፣ ለማላዉቀዉ ለማያቀኝ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አሸናፊነት እንደ አቡነ ተክልዬ በአንድ እግሬ ተተክዬ አድሬያለሁ፡፡ ለሌላ ለምንም ሳይሆን ……. የጥቁር ሰዉ ድል ድሌ ስለሆነ ነዉ ያን ማድረጌ፡፡  በዶ/ር ቴድሮስ  አሸናፊነት ኢትዮጵያ አገሬ እንኳን ደስ አለሽ! አፍርካዬ እንኳንም ደስ አልሽ! አንባቢ ሆይ ይህን በማለቴ ግን  ስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ደጋፊ አድርገህ እንዳትፈርጀኝ አበክሬ አሳስባለሁ! ከዶ/ር ቴድሮስ  አሸናፊነት ባሻገር ግን በጽሞና ሊጤን የሚገባዉ አደገኛ ሁኔታ በፖለቲካዉ መስክ ሲስተጋባ ሰንብቷል አዲስ ክስተት ባይሆንም ፡፡ ጉዳዩ ከሃገር ዉጪ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጲያዊያን ብቻ የሚመለከት የባህር ማዶ ሰዎች ግርግር  ተደርጎ መወሰድ ያለበት አይመስልም፡፡ በሃር ማዶ የተከካዉና የተቦካዉ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሲጋገር በተደጋጋሚ የሚስተዋል  ፖለቲካዊ እዉነታ ነዉ ፡፡ በተለይም በቋንቋና በብሄር ተቧድኖ  ለተቀዋሞ እና ለደጋፍ መሰለፍ  የዘዉጌ ዋልተኝነትን  (ethnic polarization) በማጦዝ  የማንወጣዉ የእርስ በርስ ጥላቻና ቀውስ ዉስጥ እየዘፈቀን መሆኑ ልብ ሊባል የሚገባዉ አደገኛ ሂደት ነዉ፡፡ እንዴት ነዉ ነገሩ፣ መጨረሻችን ምን ሊሆን ነዉ የሚያስብል ይመስለኛል፡፡ ጎበዝ ትንንሽ ክስተተቶች ናቸዉ እየሰፉ ሄደዉ የቀዉስና የእልቂት ምክንያት የሚሆኑት፡፡ የጥላቻዉ እና የመገፋፋቱ ስሜት ከምህዋረ ዜና እና ከማሃበራዊ ሚዲያዉ አልፎ  በስፖርት ማዘዉተርያዎች መጸባረቅ ጀምሯል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት መቐለ ላይ የተከሰተዉን የኳስ ሜዳ ግርግር ማስታወሱ በቂ ይመስለኛል፡፡ ግነት በሌለበት እዉነታ የኢትዮጵያዉያን የዘዉግ ክፍፍል (ethnic fractionalization) ከግለሰብ አስተሳሰብ አልፎ  ወደ ቡድናዊ ስሜት በከፍተኛ ደረጃ አድገዋል፡፡  አገራዊ ማንነት  በዘዉጌ ስሜት ተለዉጣል፡፡ ይህ ባይሆን ሁላችን ልኮራበት የሚገባ ጉዳይ  በዘዉግ ማንነት ተመዝኖ አስደንጋጭ በሆነ አከኋን ኢትዮጵያዊነት በአለም መድረክ ባልተዋረደ ነበር፡፡ ይህ እንዲሆን በርግጥም ኢትዮጵያን የሚያስተዳድራት ገዥ ሃይል በአላማ ሰርቷል ……. ተሳክቶለታልም፡፡ ከ 26 ዓመታት በኋልም ከተጓዘበት አገርን አደጋ ላይ ከሚጥል የተሳሳተ የፖለቲካ መስመር ለመዉጣት ፍቃደኛ የሆነ አይመስልም፡፡ ገዥዉ መንግስት ኢትዮጵያዊነት የሚል ስሜትን አጥብቆ  ይፈራል፡፡ ለዚህ ቀልል ማሳያ  ሚሊዮኖች በፍቅር የሚከተሉትን፣ ኢትዮጵያዊነትን የሚያከብር እና የሚዘክርን የጥበብ ሰዉን (ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን) ቃለ-መጠይቅ በዘዉጌ ማንነት አልተቃኝም በማለት መንግስት በሚቆጣጠረዉ ምህዋረ ዜና ለህዝብ እንዳይተላለፍ ከልክሏል፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር የሚያሳፍር ብቻ ሳይሆን እቺ አገር የማናት የሚስብል ጥያቄን ያጭራል፡፡ ይህን የመሳሰሉ ክስተቶች ናቸዉ ተከማችተዉ ወደ አልተፈለገ ዉዝግብና መገፋፋት የሚያመሩት፡፡ ከገባንበት አዙሪት፣ ሊመጣ ከሚችለዉ አደገኛ የእርስ በርስ ግጭትና ቀዉስ ለታደገን የሚችለዉ በህዝቦች መካከል እኩልነት፣ ፍትህ እና እዉነተኛ ፍቅር መኖር ሲችል ነዉ፡፡ የህዝቦች መስተጋብር እና ደማቅ ፍቅር የሚመሰረተው ከቂም በቀል በጸዳ ልቦና መቀራረብ ሲቻል ነዉ ፡፡ ለዚህ መሳካት በቅድምያ እዉነተኛ የእርቅ  መንፈስ በህዝቦች መካከል ሊሰፍን ይገበዋል፡፡ የስርአቱ ባለቤቶች ለ26 ዓመታት ከቀለዱት “ማን ከማን ተጣላና እናስታርቅ” ይሉት አይነት  አሰልቺ ኩሸት ተላቀዉ የኢትዮጵያን ለማዳን ሲባል በህዝቦች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ ማደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ መንግስት ከህዝብ ጋር እልህ መጋባቱን ማቆም ይኖርበታል፡፡ የመንግስት ሰዎች ከእያንዳንዱ ፖለቲካዊ ክስተት ተገቢዉን ትምህርት ወስደዉ ተገቢዉን የእርምት እርምጃ ማስከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ካለ ቅጥ እየተለጠጠ የመጣዉ የዘዉጌ ዋልተኝነት አገር የሚያጠፋና የህዝብን እልቂት የሚያስከትል አደጋን አዘሎ  እየተከተለን  መሆኑን ልንስተዉ አይገባም፡፡ ስለሆነም መንግስት የዶ/ር ቴድሮስ አሸናፊነትን ከግንቦት 20 ማድመቂያነት ባለፈ የተስተዋለዉን ተቀዋሞም አጢኖ የመግባባትና የመቀራረብ ስራዎችን ለመስራት ቢችል ባህር ማዶ ያሉ ወገኖች እና አክቲቪስት ነኝ ባዮችን ከጠርዘኝነት መስመር ወደ መሃል ለመሳብ ይችል ይሆናል፡፡ ይሄ የሚሳካዉ ግን ከዘዉግ ባሻገር በኢትዮጵያዊነት ለማሰብ የሚችል አቅም ያለዉ የመንግስት ሃይል ሲኖር ብቻ ነዉ፡፡ አሁን ያለዉን አገራዊ ቀዉስም ሆነ መጪዉን አደገኛ ሁኔታ መታገልና ማሸነፍ የሚቻለዉ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ዳርቻ ያሉ ህዝቦችን በኢትዮጵያዊነት መፈስ ማስተሳሰርና በእኩልነት ማሰተዳዳር ሲቻል መሆኑን አበክሮ  መረዳቱ ቁልፍ ጉዳይ ነዉ፡፡ ያኔ ሃቀኛ ዴሞክራሲያዊና እኩልነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያ ደምቃ ትታያለች፡፡ ያኔ በአለም መድረክ የሚገኝ ድል የጋራ ደስታችን፣ ሽፈታችንም የወል መከራችን ይሆናል፡፡ ለዚሁሉ መሳካት ግን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ማስቀደም ሆናል! *************
0 notes
ethioexplorer · 8 years
Photo
Tumblr media
የክርስቶፎር ክለኻም መጽሐፍ ወደ አማርኛ ተመለሰ ዋዜማ ራዲዮ- ባለፈው ወር The Horn of Africa: State Formation and Decay የሚል አዲስ መጽሐፍ የጻፉትና በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ታሪክ ዙርያ ተሰሚነት ያለው ትንታኔ በማቅረብ የሚታወቁት ክርስቶፈር ክላሀም ከታተመ ቆየት ያለ አንድ ሥራቸው በዚህ ሳምንት ለአማርኛ አንባቢ ተተርጉሞ ቀርቧል፡፡ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1988 ዓ. ም ለሕትመት የበቃውና በ60ዎቹ አጋማሽ የተካሄደውን አብዮትና ያስከተለውን ዉጤት በጥልቀት የሚተነትነው ይህ የክሪስቶፎር ክላኸም ቆየት ያለ መጽሐፍ Transformation and Continuity in Revolutionary Ethiopia የሚል ርዕስ ነበረው፡፡ ወደ አማርኛ የመለሱት ተርጓሚው አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ‹‹መንግሥቱ ኃይለማርያም እና አብዮቱ›› የሚል ርዕስ ሰጥተውታል፡፡ ክርስቶፎር ክለሃም ይህ መጽሐፋቸው የተጸነሰው በደርግ ጊዜ ስምንተኛው ዓለማቀፍ የኢትዮጵያ ጥናት ኮንፈረንስ ለመታደም አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት እንደነበር በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ጠቅሰዋል፡፡ መረጃ የመሰብሰብ የመስክ ሥራቸውን በስፋት ያከናወኑት ደግሞ በ1970ዎቹ መጨረሻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጋባዥ ፕሮፌሰር ኾነው ለሰባት ወራት በቆዩበት ወቅት ነበር፡፡ ደራሲው በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ባንጸባረቁት ተጨማሪ አስተያየት ኢትዮጵያ ዉስጥ በአመዛኙ ጉዳት የለሽ መረጃዎችን የመደበቅና በምስጢር የመያዝ አባዜ እንደሚስተዋል፣ የፈጠራ ታሪኮችንና አፈ ታሪኮችን እውነት አድርጎ የመቀበል ባህል በስፋት እንደሚታይ ይህም በምርምር ሥራቸው ላይ ተግዳሮት ኾኖ እንደቆየ ጠቅሰዋል፡፡ በደርጉ ሊቀመንበር የአስተዳደር ዘይቤ ላይ ባሰፈሩት ጥቅል አስተያየት ደግሞ ደራሲው የሚከተለውን ብለዋል፤ ‹‹የመንግሥቱ ኃይለማርያም የአመራር ጥበብ ብዙዎች እንደሚገምቱት የካስትሮ ወይም የኦል ሱንግ ግልባጭ አልነበረም፤ መንግሥቱ ሙሉ በሙሉ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ፍጹማዊነት ወርሰዋል፡፡ የንጉሡን ቤተ-መንግሥት ከነሙሉ አገልጋዮቻቸው የወረሱት መንግሥቱ እንደ ቀ.ኃ.ሥ ሁሉ እርሳቸውም ከተራው ሕዝብ በመነጠል በርቀት እንዲከበሩና እንዲፈሩ ሆነዋል›› ሲሉ የኮሎኔሉን የአስተዳደር ዘይቤ ተችተዋል፡፡ የዋቢ ጽሑፎችን መዘርዝር ጨምሮ 350 ገጾች ያሉት ይህ መጽሐፍ በአስር ምዕራፎች ነው የተዋቀረው፡፡ በይበልጥ ከአብዮቱ አንስቶ እስከ ኢህድሪ ምሥረታ ያሉ አንኳር ጉዳዮች ተዳሰውበታል፡፡ የብሔር ጥያቄዎች ማቆጥቆጥ፣ አብዮቱና የምዕራባዊያን ምላሽ፣ የግብርና ምርታማነት ቀውስ፣ የትምህርት እድገት፣ የከተሞች ቁጥጥርና አገዛዝ በደርግ ምን ይመስል እንደነበር መጽሐፉ ይተነትናል፡፡ በመጽሐፉ መደምደሚያ ደርግ ሁሉንም ነገር ብቻውን ለመፈጸም ያደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል፣ አንድነትና ልማትን ለማሳካት የደከመው ድካም ሁሉ ያሰበውን አንድነትም ኾነ ልማት እንዳላመጣለት፣ ይልቁንም ተቃውሞዎች እንዲበረቱበት እንዳደረገው ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ‹‹የአብዮቱ መንግሥት ዋና ችግር በመ���ፉ ከሚጨብጠው እፍኝ ስኬት ይልቅ በርቀት ለመያዝ የሚመኘው ግብ ሰፊና ከአቅሙ በላይ መሆን›› እንደነበር አውስተዋል፡፡ ሥርዓቱ የግብርና ልማትና ማኅበራዊ ሽግግርን ለማምጣት ባለው አቅም ሁሉ ቢጥርም የረሀብን አደጋ እንኳ ማስቀረት እንዳልቻለ ጠቁመዋል፡፡ ከአርሶ አደሩ የሚገኘው ምርትና የሚሰበሰበው ግብአት ለመንግሥት ኢንዱስትሪዎች ድጋፍና ለወታደራዊ ወጪ መዋሉ የሥርዓቱ ዉድቀት መነሻ እንደሆነም ተንትነዋል፡፡ የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነት ለመጠበቅ የተደረገው የቁጥጥርና የማማከል ሥራ ወታደሩን እረፍት የነሳው በመሆኑና ከሰሜን ወደ ደቡብ እየሰፋ የመጣ ተቃውሞ በመፈጠሩ ሳይሳካ እንደቀረም አብራርተዋል፣ በመጽሐፋቸው፡፡ በተጨማሪም ንጉሡ ‹‹የኤርትራን ችግር ለመፍታት የወሰዱት የዉህደት እርምጃ የመንግሥታቸውን ፖለቲካዊ ድክመት ያሳየ መሆኑ በአብዮቱ ዉጤት ታይቷል›› የሚሉት ፕሮፌሰር ክለኻም ደርግ ሁሉንም ችግሮች በተማከለ መንግሥታዊ ቅርጽ ምላሽ ለመስጠት መሞከሩ እንዲበተን አድርጎታል ይላሉ፡፡ ክርስቶፎር ክለኻም ይህን መጽሐፋቸውን መታሰቢያ ያደረጉት በግንቦት 1980 ድንገት በሞት ለተለያቸው ጥበቡ ደርቤ ለሚባል የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ3ኛ ዓመት የስታትስቲክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ ነው፡፡
0 notes