#ሠሙነሕማማት
Explore tagged Tumblr posts
lijmesfin · 6 years ago
Photo
Tumblr media
~~~የ #ሠሙነሕማማት #ሐሙስ ~~~ (ፅሁፍ ከመልዐከ ሰላም አባ ገብረሚካኤል fb page የተወሰደ) ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተ ክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ 1.ሕጽበተ እግር ይባላል፡፡ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡ /ዮሐ. 13፤4-15/ 2.የጸሎት ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፡፡ /ማቴ. 26፤36፣ ዮሐ. 17፤1/ 3.የምሥጢር ቀንም ይባላል፡፡ ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷል፡፡ ይኸውም “ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚ���ረሰው ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ “ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ። “ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ” በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፡፡ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም፡፡ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡ 4.የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳ ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ /ሉቃ. 22፤18-20/ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡: 5.የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱም ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ.15፤15/ ከባርነት ነጻ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል፡፡ /ማቴ 26፤17-19/ 6.አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ፡፡ https://www.instagram.com/p/Bwqi5KJAAuH/?utm_source=ig_tumblr_share&igshid=iy1gfa29npw
0 notes
lijmesfin · 6 years ago
Photo
Tumblr media
#ሠሙነሕማማት ~~~ ሐሙስ ~~~~~~ #ሕጽበተእግር ~~~~~~ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡ (ዮሐ. 13፤4-15) Jesus Washes the Disciples ‘ feet The icon depicting our Lord washing the feet of His disciples is a beautiful example of love and humility. We are taught by the hymns of the Church: "The Savior and Master, ever leading us to divine exaltation, in His actions revealed to us the humility that raises us on high. For with His own hands, He washed the feet of the disciples." As Jesus washes the feet of His disciples, we have both a symbol of baptism and an example of service. This becomes more profound when we realize that in Jesus, God in the flesh renders humility as an expression of stewardship. As Christians, we are bathed and cleansed by Christ in the Sacrament of Holy Baptism and Holy Confessions. The only way for God to assist us in actualizing the likeness we have in Him is to guide us in developing His unselfishness in us. Giving is not for God’s benefit, but for our own. He waits patiently for us to learn to give. Humankind may be transformed into His likeness by the process of STEWARDSHIP. We need to be honest with God. Like our Time and Talents, our Treasure is also a gift from God. He makes it possible for us to acquire such treasurer. Obtaining what we believe to be our own material possessions, our treasures are actually entrusted to our care by God. As Orthodox Christians, we have the responsibility to our Lord to support and make possible the perpetuation of the ministry of His Church in the world. Our response to this call is by giving in an open, direct, and honest manner. The Lord puts forth many examples of humility and love. As in the example of our Lord washing the feet of His disciples, Church leadership must also set the example of ministering with humility. It is our STEWARDSHIP obligation and privilege to serve God and our fellow humankind. This is the life of the Church in all Her mystical, catechetical, and pastoral expressions. ( #John13 :1-17) https://www.instagram.com/p/Bwqg-TLAYQP/?utm_source=ig_tumblr_share&igshid=9xur76j0szxt
0 notes
lijmesfin · 6 years ago
Photo
Tumblr media
#ሠሙነሕማማት ... 12 በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ። 13 ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። 14፤ መልሶም፡— ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ፡ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ። 15፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤ 16፤ ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም። 17፤ አስተማራቸውም፡— ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት፡ አላቸው። 18፤ የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ። (የማርቆስ ወንጌል 11 ፤ 13) #Mark11:12 And on the morrow, when they were come from Bethany, he was hungry: 13: And seeing a fig tree afar off having leaves, he came, if haply he might find any thing thereon: and when he came to it, he found nothing but leaves; for the time of figs was not yet. 14: And Jesus answered and said unto it, No man eat fruit of thee hereafter for ever. And his disciples heard it. 15: And they come to Jerusalem: and Jesus went into the temple, and began to cast out them that sold and bought in the temple, and overthrew the tables of the moneychangers, and the seats of them that sold doves; 16: And would not suffer that any man should carry any vessel through the temple. 17: And he taught, saying unto them, Is it not written, My house shall be called of all nations the house of prayer? but ye have made it a den of thieves. #Himamat (at Debreselam Medhanealem EOTC Minnesota) https://www.instagram.com/p/BwjvX-FgVXe/?utm_source=ig_tumblr_share&igshid=uqqidzcn6rhq
0 notes